Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

ddot

District Department of Transportation

Amharic (አማርኛ)

This page contains information about the Department of Transportation for Amharic speakers.

የኤጀንሲው ስም: የዲስትሪክቱ የመገናኛ ዲፓርትመንት (District Department of Transportation)

ተልእኮ:

እንኳን ወደ የዲስትሪክቱ የመገናኛ ዲፓርትመንት በደህና መጡ! ዲዲኦቲ (DDOT) በአገሪቱ መዲና ፣ የላቀ ዘላቂነት ባላቸው የጉዞ ልምዶች፣ የላቀ ደህንነት ባላቸው ጎዳናዎች፣ እና አብላጫ ባለው የንብረቶች እና አገልግሎቶች አቅርቦት በመጠቀም፣ የላቀ የኑሮ ጥራት ለማምጣት ቆርጦ ተነስቷል። ለዚህ ራእይ ማዕከል የሆነው፣ በከተማይቱ ለአንድ ሰው መንዳትን (single occupancy driving) የመጪው ትውልድ አማራጮች በማቅረብ የሀይል ብቃት (energy efficiency) እና ዘመናዊ መጓጓዣ ማዳበር ነው። ተልእኮ፡ የዲዲኦቲ (DDOT) ተልእኮ፣ የሰዎችን እና ንብረቶችን ደህንነት በጠበቀ፣ በተመጣጣኝ ዋጋ እና ምቹ በሆኑ መንገዶች- የዲስትሪክቱ ተፈጥሮአዊ፣ አካባብያዊ እና ባህላዊ ሀብቶች በጠበቀ እና ባሻሻለ መንገድ ሁሉን-አቀፍ የሆነ ዘላቂ የመገናኛ ሲስተም ማዳበር እና መጠበቅ ነው።

ዋና ዋና ፕሮግራሞች:

ዲዲኦቲ (DDOT) በ 6 ክፍሎች እና የዳሬክተር ቢሮ የተከፈለ ነው። እያንዳንዱ ክፍል የዲዲኦቲ (DDOT) ን ጠንካራ እና ቅይጥ ፕሮግራሞችን የማስተዳደር ሀላፊነት አለው።

የመሰረተ-ልማት እና ፕሮጀክት ማኔጅመንት አስተዳደር (The Infrastructure and Project Management Administration)፣ በዲስትሪክቱ የመንገዶች፣ ድልድዮች፣ የትራፊክ ምልክቶች እና የጠባብ/ጛሮ መንገዶች ፕሮጀክቶችን ዲዛይን የማድረግ፣ የምህንድስና እና የመገንባት ሀላፊነት አለው። የአይፒኤምኤ (IPMA) በጣም ዝነኛ የሆኑ ፕሮግራሞች፣ የአናኮስትያ ዋተርፍሮንት ተነሳሽነት (Anacostia Waterfront Initiative)፡ የ11ኛው መንገድ ድልድይ ያጠቃለለ የአናኮስትያ የወንዝ ዳርቻ አከባቢው የመገናኛ መሰረተ-ልማት በማቀድ፣ በመንደፍ እና በመገንባት ለውጥን የማምጣትን ተነሳሽነትን ያጠቃልላል።

የፖሊሲ እቅድ እና የዘለቂነት አስተዳደር (The Policy Planning and Sustainability Administration)፣ የማልቲ-ሞዳል የፕሮግራም እድገትን (multi-modal program development) የሚመራ ሰፊ ስልታዊ ግቦችን እና እነዚህን ዓቦችን ተግባር ላይ ለማዋል የሚያስፈልጉ ፖሊሲዎች ያቋቁማል፣ በዕቅድ ክለሳ እና ፈቃድ በመስጠትም መሟላቱን ያረጋግጣል። ፒፒኤስኤ (PPSA)፣ ከ1800 በላይ የሚሆኑ ብስክሌቶች በአቅራብያዎ እንደሚገኙ የሚያደርግ የካፒታል ባይክሼር ፕሮግራም (Capital Bikeshare program) እና፣ ሙቭዲሲ (MoveDC) የተባለው ለከተማይቱ የመገናኛ የወደፊት ጠንካራ አሰራር መሰረት ያደረገ ዕቅድ ለማዳበር የሚሰራ በዲዲኦቲ (DDOT) የሚመራ የትብብር ጥረትን የማስተዳደር ሀላፊነት አለው። ክልላዊ ፖሊሲዎች ለማዳበር ደግሞ ከሌሎች የመገናኛ ኤጀንሲዎች ጋር ይሰራል።

በእድገት ላይ ያለ የመገናኛ አገልግሎቶች አስተዳደር (The Progressive Transportation Services Administration) ለዋሺንግተን ሜትሮፖሊታንት አካባቢ የመገናኛ ባለስልጣን (ዳብሊውኤምኤቲኤ)(Washington Metropolitan Area Transit Authority (WMATA)) ፣ መውአለ ነዋይን፣ የፖሊሲ ሀሳቦችን እና የማስተባበር አገልግሎቶች ያቀርባል፣ የአገራችን ዋና ከተማ ነዋሪዎች እና ጎብኚዎች፣ ወደ መድረሻቸው በፍጥነትን እና አስተማማኝነት ባለው መንገድ እንዲደርሱ የሚረዱ በተለያዩ የትራንዚት አገልግሎቶች መርካት እንዲችሉ ያደርጋል። ፒቲኤስኤ (PTSA) የትምህርት-ቤት ትራንዚት ድጎማ ፕሮግራም (School Transit Subsidy Program)፣ የአዛውንቶች እና አካል ጉዳተኞች ፕሮግራም (Elderly and Persons with Disabilities Program)፣ ተዟዟሪ አገልግሎት (the Circulator service) ይቆጣጠራል፤ የዲዲኦቲ (DDOT) በጣም ደስ የሚል አዲስ ፕሮግራም፣ ዚ ስትሪትካር (the Streetcar)፣ ለማስተዋወቅ ደግሞ በዝግጅት ላይ ይገኛል።

ህዝብ ቦታ ደንቦች አስተዳደር (The Public Space Regulations Administration) የህዝብ ቦታ ህጎች እና ደንቦች ተግባር ላይ እንዲውሉ ያደርጋል፣ ስራዎች በዲዲኦቲ (DDOT) መመዘኛ መሰረት እየተሰሩ እንደሆነ ለማረጋገጥ በህዝብ ቦታ ፈቃድ የተከናወኑ ሁሉም የህዝብ ቦታ ስራዎች ይፈትሻል። በህዝብ ቦታ ላይ ስራ መስራት ለሚፈልጉ ነዋሪዎች ፈቃዶች እንዲሰጧቸው በፒኤስኣርኤ (PSRA) ቢሮዎች ማመልከት ይችላሉ። ፒኤስኣርኤ (PSRA) በተጨማሪ ቶፕስ (TOPS) ተብሎ በሚጠራው የመገናኛ ኦንላይን ፈቃድ ሲስተም (Transportation Online Permit System) በመጠቀም የብሎክ ፓርቲ ምዝገባ (Block Party Registration) ሂደት ያስተዳድራል።

የመገናኛ ኦፐሬሽን አስተዳደር (The Transportation Operations Administration)፣ መንገዶች፣ የእግረኛ መንገዶች፣ የትራፊክ ማረጋግያ መሳርያዎች፣ የመንገድ መብራቶች፣ የፓርኪንግ ሚተሮች ይጠብቃል፣ ደህንነት ያለው እና ለተጠቃሚ-ደስ የሚያሰኝ የመገናኛ ሁኔታ እንዲኖር ያደርጋል። ቲኦኤ (TOA) የ24/7 የትራፊክ ማኔጅመንት ማዕከል ያካሂዳል፣ ጭንቅንቅን ይከላከላል፣ በትራፊክ መከላከያ ኦፊሰር እና ትምህርትቤት የመሸጋገር ዘበኛ ፕሮግራም (Traffic Control Officer and School Crossing Guard program) በመጠቀም የእግረኛ ደህንነት ያረጋግጣል፣ መንገዶች፣ የእግረኛ መንገዶች እና የተበላሹ የትራፊክ ምልክቶች በየቀኑ ይጠግናል።

የከተማ ደን አስተዳደር (The Urban Forestry Administration) የተሻለ የአየር ጥራት የሚሰጡ፣ ጎርፍ የሚያሳንስ የተሻለ የመሬት ውሀ መያዝ
የሚችሉ፣ እና የሙቀት ልቀት የሚቆጣጠሩ ጤናማ ዛፎች በመጠበቅ፣ የዲስትሪክቱ አረንጓዴ ቦታ ያስተዳድራል። የዛፎች ተከላን ለማበረታታት፣ የቀለጠፈ
ምልመላና ትንሽ ዛፍ የመቁረጥ አገልግሎቶች ለማግኘት እና አደገኛ ወይም ጤናማ ያልሆኑ ዛፎች ከህዝብ ቦታ ለማስወገድ፣ ነዋሪዎች በከተማ ደን
አስተዳደር (Urban Forestry Administration) መተማመን ይችላሉ።

የዳሬክተር ጽሕፈት ቤት (The Office of the Director) የድንገተኛ ማኔጅመንት፣ የግንኙነቶችን እና የደንበኛ አገልግሎት ክፍላችን ያጠቃለሉ የተለያዩ
የአስተዳደር ስራዎች ይከታተላል። በተጨማሪ፣ ከሲቪላዊ መብቶች ጋር የተያያዙ የማሟላትን ፕሮግራሞች እና ፖሊሲዎች የሚያስተዳድረው የሲቪል
መብቶች ጽሕፈት ቤት (Office of Civil Rights) ወይም ኦሲኣር (OCR) ያጠቃልላል። ይሔ፣ አነስተኛ እና የዝቅተኛ ድርጅቶች የሚያረጋግጥ እና
በመገናኛ ግንባታ ኮንትራት ለማግኘት እንዲወዳደሩ የሚያግዝ አነስተኛ እድል ያላቸው ንግዶች ኢንተርፕራይስ ፕሮግራም (Disadvantaged Business
Enterprise Program) ያጠቃልላል። ኦሲኣር (OCR) በተጨማሪ፣ በዲሲ ሰብአዊ መብቶች ሕግ (DC Human Rights Act)፣ የዲሲ የቋንቋ አቅርቦት
ህግ (DC Language Access Act) እና የ1964ቱ የታይትል VI የሲቪል መብቶች ህግ (Title VI of the Civil Rights Act of 1964) መሰረት፣ ከሕዝብ
የቋንቋ እገዛ ጥያቄዎች እንዲሁም አድሎ ላይ የተመሰረተ አቤቱታዎችን ሂደት ለማስተናገድ ጥያቄዎች ይቀበላል።

አገልግሎቶች:

 የትምህርት-ቤት ትራንዚት ድጎማ ፕሮግራም (School Transit Subsidy Program): የትምህርት-ቤት ትራንዚት ድጎማ ፕሮግራም (School
Transit Subsidy Program) ወደ ትምህርት-ቤት ሲሄዱና ሲመለሱ ሜትሮባስ፣ ሜትሮ ረይል ወይም ዟሪን (ሰርኩሌተር) ለሚጠቀሙ
የዲስትሪክት ተማሪዎች ቅናሽ ዋጋ ይሰጣል። በአሁኑ ግዜ፣ ተማሪዎች $30 ዶላር በመክፈል ለወር የሚያገለግል ይለፍ መግዛት ይችላሉ- ይሔም
በዲስትሪክቱ ውስጥና በአቅራብያ የሚገኙ የሜትሮ ረይል ጣብያዎች (ለምሳሌ፣ ሳውዘርን ኣቨኑ፣ ሲልቨር ስፕሪንግ፣ ካፒቶል ሃይትስ፣ ፍሬንድሺፕ
ሃይትስ፣ እና ነይለር ሮድ) ለመጓዝ የሚጠቅም፣ 10-ጉዞ የባቡር ይለፍ እንደ የወር ይለፍ ዓይነት ገደብ ያለው በ $9.50 ፣ ኤሌክትሮኒክ የ10-ጉዞ
የአውቶቡስ ይለፍ በ$7.50 – ዲሲ ዋን ካርድ (DC One Card) ብቻ፣ እና 10 የአውቶቡስ ሳንቲሞች በ$7.50 መግዛት ይችላሉ። ይሔ
ፕሮግራም የዲሲፒኤስ (DCPS) ትምህርት-ቤት፣ የቻርተር እና የግል ትምህርት-ቤቶች የሚማሩ ተማሪዎች እና በዲስትሪክቱ ባሉ የትምህርት
ፕሮግራሞች የሚሳተፉ ተማሪዎችን ያገለግላል። Click here to enter text.

 የአዛውንቶች እና አካል ጉዳተኞች ፕሮግራም (Elderly and Persons with Disabilities Program): አዛውንቶችን እና አካል ጉዳተኞችን
የመገናኛ አገልግሎት ለመስጠት እንዲችሉ፣ በዲስትሪክት ኦፍ ኮሎምብያ የሚሰሩ ለትርፍ የማይሰሩ ድርጅቶች መኪና መግዣ የሚሆን የገንዘብ
ድጋፍ የሚያሰጥ፣ በፌደራል ፋንድ የሚደረግ፣ ፕሮግራም ነው።

 ዟሪ (ሰርኩሌተር) (Circulator): የሰርኩሌተር ልዩ ቀይ አውቶቡሶች በከተማ አከባቢ ካሉ ሌሎች የህዝብ ትራንዚት የተለዩ ናቸው- ከዝቅተኛ
ወለል ጋር፣ ትላልቅ መስኮቶች፣ እና በቀላሉ መውረድ እና መሳፈር የሚያስችሉ ብዙ በሮች አሏቸው፣ ሰርኩሌተር በየ10 ደቂቃዎች ትመጣለች፣
እያንዳንዱ ጉዞ $1 ብቻ ያወጣል። በተጨማሪ፣ ስማርትትሪፕ (SmartTrip) ካርድ የሚጠቀሙ የሜትሮረይል ተጠቃሚዎች ቅናሽ የመዘዋወርያ
ዋጋዎች ማግኘት ይችላሉ። ለመንገድ ካርታ እና ሌላ የአገልግሎት መረጃ እባክዎን DCCirculator.com ይግብኙ።

 የዲሲ ስትሪትካር (DC Streetcar): የዲሲ ስትሪትካር (DC Streetcar) በዲስትሪክት ውስጥ ለሚካሔደውን ጉዞ ለነዋሪዎች፣ ለሰራተኞች እና
ለጎብኚዎች በጣም የቀለለ ያደርገዋል፣ ላሉት የትራንዚት አማራጮች ተጨማሪ ይሆናል። ስትሪትካር (The Streetcar)፣ ሰፈሮች በዘመናዊ፣
ምቹ እና ሳቢ የሆነ የመገናኛ አማራጭ ያገናኛል፣ አዲስ የትራንዚት ተጓዦች ለመሳብ እና ለማግኘት ጥራት ያለው አገልግሎት ያቀርባል፣
በተጨማሪ የከተማ ውስጥ ኣጭር የመኪና ጉዞዎች፣ የፓርኪንግ ፍላጎቶች፣ የትራፊክ መጨናነቆች እና የአየር ብክለት ይቀንሳል። ስለ የዲሲ
ስትሪትካር (DC Streetcar) አዳዲስ መረጃ ለማግኘት www.dcstreetcar.com ይጎብኙ።

 ሙቭዲሲ (MoveDC): በዲስትሪክቱ የሁሉንም የመገናኛ ዘዴዎች ግምት ውስጥ ያስገባ የተቀነባበረ የበርካታ-ዘዴዎች የረጅም ግዜ የመገናኛ
ዕቅድ (multimodal long range transportation plan) ለማዳበር የዲዲኦቲ (DDOT) ተነሳሽነት ነው። በሙቭዲሲ (MoveDC) ዕቅድ
ግዜ፣ ከአስፈላጊ የክልል ትሥሥሮች በተጨማሪ፣ መላው የዲስትሪክት ኦፍ ኮሎምብያ የመገናኛ መረብ፣ ግንዛቤ ውስጥ ይገባል። እያንዳንዱ
የመገናኛ ዘዴ እንደ የበርካታ-ዘዴዎች የመገናኛ ዕቅድ (multimodal transportation plan) ማዳበርያ አካል ተወስዶ ይመዘናል፣ ግምት
ውስጥም ይገባል። ለተጨማሪ መረጃ ወይም በፕሮግራሙ ለመሳተፍ እባክዎ http://www.wemovedc.org/ ይጎብኙ።

 ካፒታል ባይክሼር (Capital Bikeshare): ይሔ ዝነኛ የብስክሌት መጋራት (ባይክሼሪንግ) ፕሮግራም፣ ከ1800 በላይ የሆኑ ብስክሌቶች
በአቅራብያዎ እንደሚገኙ ያደርጋል። ካፒታል ባይክሼር (Capital Bikeshare)፣ በዋሺንግተን ዲሲ እና አርሊንግተን፣ ቨርጂንያ ውስጥ ከሚገኙ
ከ110 በላይ ከሚሆኑ ጣብያዎች መምረጥ ያስችልዎታል፣ ለመድረሻዎ ቅርብ ወደ ሆነ ጣብያ መመለስም ይችላሉ። የባይክሼር ቦታዎች ይሆናሉ
ተብለው ስለታቀዱ ቦታዎች አስተያየት ለመስጠት፣ እባክዎ በ[email protected] ኢ-ሜይል ያድርጉ። ስለ ፕሮግራሙ ተጨማሪ
መረጃ ቢፈልጉ እባክዎ http://capitalbikeshare.com/ ይጎብኙ።

 የልዩ ዛፎች ፈቃዶች (Special Tree Permits): ማንኛውም ሰው፣ ኗሪም ይሁን ኮንትራክተር፣ በፓብሊክ-ራይት-ኦፍ-ወይ (Public Right-of-Way) ውስጥ፣ የህዝብ መንገድ ዛፍ (የሚተክል፣ የሚመለምል ወይም የሚቆርጥ፣ መጀመርያ ከመገናኛ ዲፓርትመንት የከተማ ደን አስተዳደር (ዩኤፍኤ) (Department of Transportation's Urban Forestry Administration (UFA)) ፈቃድ ማግኘት አለበት።
o በድህረገጽ፣ በመገናኛ ኦንላይን ፈቃድ መስጫ ሲስተም (ቶፕስ) (Transportation Online Permitting System (TOPS)) በመጠቀም ወይም ወደ የህዝብ ቦታ ፈቃድ ቢሮ (the Public Space Permit Office) ሔደው በሁለተኛ ፎቅ፣ በፈቃድ ቢሮው ጎን ባለው አዳራሽ ባሉ ኪዮስኮች አንዱ ላይ በመሔድ የፈቃድ ጥያቄዎን ያቅርቡ፤ አድራሻው፡
የዲስትሪክት የመገናኛ ዲፓርትመንት (District Department of Transportation)
የህዝብ ቦታ ፈቃድ ቅርንጫፍ (Public Space Permit Branch)
1100 4th Street SW
Washington, DC 20024
o ዩኤፍኤ (UFA) የፈቃድ ማመልከቻ እንደተደረገ የሚያሳይ ማሳሰብያ ከደረሰው በኋላ፣ የቀረበው የቦታ ዕቅድ እና ሌሎች ነገሮች ወደሚመዝነው፣ ወደ ተገቢው )የዛፍ ባለሙያ(አርቶትሪስት) ይመደባል፣ የተጠየቀው የስራ አይነት እስከምን ያክል እንደሆነ ለማጣራት ወደ ቦታው ሄዶ ሊጎበኝ ይችላል።
o የተመደበው የዛፍ ባለሙያ(አርቶትሪስት) ስለ ማመልከቻው ተገቢ ውሳኔዎች ይሰጣል።
ማሳሰብያ፡ የከተማ ደን አስተዳደሩ (Urban Forestry Administration) ከህዝብ ዛፎች ጋር የተያያዙ ወይም ተጽዕኖ የሚያሳድሩ የህዝብ ቦታ ፈቃዶችን በሙሉም ይሁን በከፊል የመከልከል መብቱ የተጠበቀ ይሆናል።

 የዛፍ አገልግሎት ጥያቄዎች (Tree Service Requests): ድንገተኞችን፣ መመልመሎች፣ ማስወገዶች እና መትከሎችን ሪፖርት ማድረግ የሚያጠቃልሉ የመንገድ ዛፍ አገልግሎቶች ለመጠየቅ በ311 ይደውሉ፣ ወይም 311 Online ንን ይጎብኙ።
በሚከተለው የግዜ-ሰሌዳ መሰረት ጥያቄዎት ይመለሳል፡
o የድንገተኛ ጥያቄዎች— በ72 ሰዓታት ውስጥ
o መደበኛ የመጠገኛ ጥያቄዎች — ፍተሻ በ30 ቀናት ውስጥ
o መትከል፡ ከኖቨምበር እስከ ሜይ፣ በየዓመቱ (ጥያቄዎን በጁን 15 ያስረክቡ)
o መመልመሎች እና ማስወገዶች ፡ ለመጨረስ እስከ 9 ወራት

 ካኖፒ ኪፐር አዶፕት-ኤ-ትሪ ፕሮግራም (Canopy Keeper Adopt-A-Tree Program): ዛፍን በሀላፊነት መውሰድ ተፈጥሮን እንዳ ቤተሰብ አባል የማድረግያ ዋነኛ መንገድ ነው። በቤት-ንብረትዎ አቅራብያ የተተከሉ አዳዲስ ዛፎች ለማትረፍ የርሶን ድጋፍ ይፈልጋሉ! ነዋሪዎች እና ድርጅቶች ንብረታቸው እስከ መንገዱ ድረስ የመጠበቅ ሀላፊነት አላቸው፤ DCMR rule 21-702 ይመልከቱ። ከታች ያለው ስምምነት በማስረከብዎ፣ ዲዲኦቲ ትሪስ (DDOT Trees) ነጻ ዘገምተኛ-በማንጠብጠብ ውሀ የሚያጠጣ መሳርያ (slow-drip watering device) በመስጠት ያግዛል። ከተተከለ በኋላ ለሚኖሩ 2 ዓመታት፣ የሚከተሉትን ለማድረግ ይስማማሉ፡ o ከጸደይ (ከስፕሪንግ) መፈንደቂያ እስከ ክረምት (ዊንተር ) ቅዝቃዜ ድረስ መሳርያዎን፣ በሳምንት አንዴ 10 ጋሎን ውሀ ይምሉት። o ከተቻለ 2-4” ጥልቀት ያለው ማዳበርያ ያድርጉ፣ ማዳበርያው ከትራንኩ ራቅ ያድርጉት o አረም እና ግርድ ከመትከያ ቦታ ያጽዱ o ማንኛውም የአገልግሎት ፍላጎት ካለ በድህረ-ገጽ 311.dc.gov ወይም 311 በመደወል ሪፖርት ያድርጉ ስምምነትዎን በሚከተሉት መንገዶች ያስረክቡ፡ ኦንላን (Online): የካኖፒ ኪፐር ማመልከቻ (Canopy Keeper Application ) በፎርሙ ሥር በሚገኘው “ሳብሚት” (“submit”) የሚል ቁልፍ በመምረጥ ያስረክቡ። በፖስታ፡ የከተማ ደን አስተዳደር (Urban Forestry Administration) የዲስትሪክት የመገናኛ ዲፓርትመንት (District Department of Transportation) 55 M Street, SE, Suite 600 Washington, DC 20003

 የመኖርያ ፓርኪንግ አቤቱታዎች (Residential Parking Petitions): የአርፒፒ (RPP) ፕሮግራም በተሰየሙ ብሎኮች ለሚኖሩ ተሳታፊ ነዋሪዎች የመንገድ-ላይ ማቆሚያ(ፓርኪንግ ) ገደብ ያደርጋል። ለሌሎች ሰዎች ፓርኪንጉ የሁለት ሰዓት ገደብ ይኖረዋል። ዜጎች፣ አቤቱታ
በማቅረብ፣ 4100 የመኖርያ ብሎኮች በዚህ ፕሮግራም እንዲካተቱ አድርገዋል። ለፈቃድ ፓርኪንግ (permit parking) የተሰየሙ መንገዶች ለመፈለግ በመኖርያ ፈቃድ ፓርኪንግ ብሎክ ዳታ ኢንኳይሪ (Residential Permit Parking Block Data Inquiry) ዳታቤዝ በhttp://ddotfiles.com/db/RPP/rpp.php መፈለግ ይቻላል። ይሔን ለመጠቀም፣ እባክዎ የመዱን ስም ያስገቡ። ኤስቲ (ST) ወይም ኤቪኢ (AVE) የሚሉ ተቀጥያዎችን ማስገባት የለብዎትም። የመንገዱ ስም በሙሉ ወይም በከፊል ማስገባት ይቻላል። የብሎክ እና ዋርድ ቁጥሮች የማስገባት እና ያለማስገባት አማራጭ የርሶ ነው፣ ቢያስገቧቸው ግን ፍለጋውን በማጥበብ ሊያግዙ ይችላሉ። መንገድዎ በዝርዝሩ ከሌለ፣ የአቤቱታ ቅጹን በመጫን ዲዲኦቲን (DDOT) የፈቃድ ፓርኪንግ ፕሮግራም እንዲያነሳሳ አቤቱታ ማቅረብ ይቻላል። ማመልከቻው ማዘጋጀት ላይ ድጋፍ ከፈለጉ፣ እባክዎ የደንበኛ አገልግሎት በ(202) 673-6813 ይደውሉ።

 የአካል ጉዳተኛ ፓርኪንግ ፕሮግራም (Disability Parking Program): የመንገድ-ላይ ፓርኪንግ፣ አካል ጉዳተኞች ለሆኑ ነዋሪዎች እና ጎብኚዎች ምቹ እንዲሆን የሚያደርጉ ዲስትሪክቱ የተለያዩ ፕሮግራሞች አሉት። በነጠላ ቤተሰብ (በሲንግል ፋሚሊ) መኖርያ የሚኖሩ እና አንዳንድ ሌሎች መመዘኛዎች የሚያሟሉ አካል ጉዳተኛ የሆኑ ነዋሪዎች፣ በመንገድ ላይ ለርሶ የፓርኪንግ ቦታ እንዲመደብሎት ማመልከት ይችላሉ። ስለዚህ ፕሮግራም ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት እና የተመደበ ቦታ እንዲሰጥዎት ለማመልከት እባክዎ በ [email protected] ያግኙን።

 አዲስ የእግረኛ መንገድ መዘርግያ ጥያቄዎች (New Sidewalk Installation Requests): የከንቲባው የመላው ከተማ የጥሪ ማዕከል (Mayor's Citywide Call Center) በ 311 (202-727-1000) በመደወል ወይም በኦንላይን በዲስትሪክት መንግስቱ የአገልግሎት መጠየቅያ ማዕከል (Service Request Center) የአገልግሎት መጠየቅያ በመሙላት የእግረኛ መንገድ ጥገና አገልግሎቶች መጠየቅ ይቻላል። እባክዎን ችግር ያለው የእግረኛ መንገዱን ትክክለኛ ቦታ ይጠቁሙ፣ የእግረኛ መንገዱ ዓይነት (እሱም፣ ሰሜንቶ (ኮንክሪት)፣ ጡብ ወይም ሌላ ተነጣፊ ነገር) ይግለጹ። ጉዳቱ ምን ያክል እንደሆነ መረጃ ይስጡ (እሱም፣ የተሰነጠቀ ነው የተሰበረ፣ የሌሉ ጡቦች አሉ፣ የዛፍ ስሮች እግረኛ መንገዱን ከታች ወደ ላይ እየገፉ ናቸው)። በትራኪንግ ሲስተሙ (tracking system) የአገልግሎት ጥያቄ ይቀመጣል፣ የአገልግሎት ጥያቃ ቁጥርም ማግኘት ይኖርቦታል።
ምላሽ የማግኛ የጊዜ-ሰሌዳ :
o ፍተሻ (Investigation): 1-10 የስራ ቀናት
o ግዚያዊ (ድንገተኛ) ጥገናዎች፡ እስከ 15 የስራ ቀናት
o ቋሚ እልባት የፍተሻው ውጤቶች ላይ መሰረት ያደርጋል
o ቋሚ ጥገናዎች የረዘመ የጊዜ ገደብ ይፈልጋሉ፣ የገንዘብ መገኘት እና አለመገኘት ጋርም ይያያዛሉ
ማሳሰብያ: የ”አዲስ” የእግረኛ መንገድ ጥያቄ በብሎክዎ ከሚኖሩ አብዛኛዎቹ/አብላጫ ነዋሪዎች አቤቱታ እና ህዝባዊ ሂሪንግ (public hearing) ይፈልጋል።

 የፍጥነት መቀነሻ ሻኛ የመዘርጋት ጥያቄዎች (Speed Hump Installation Requests): የፍጥነት መቀነሻ ሻኛ መጠቀም፣ የመኪኖች መጠቀም አሉታዊ ውጤቶችን ሊቀንስ፣ የነጂ ባሕሪ ሊቀይር፣ ለእግረኞች እና መኪና ለማይጠቀሙ የመንገድ እና ጎዳና ተጠቃሚዎች ሁኔታ ሊያሻሽል ይችላል። በነዋሪዎች ዘንድ፣ “በሎካል” መንገዶች ትራፊክ ለማረጋጋት ያለው ፍላጎት ለሟሟላት፣ ዲዲኦቲ(DDOT) የግለሰቦች፣ የማህበረሰብ ቡድኖች እና የኤኤንሲዎች (ANCs) ጥያቄዎች እንዴት መመለስ እንዳለበት የሚያመለክቱ መመርያዎች ሰርተዋል። በተወዳዳሪ ብሎክ ወይም የመንገድ ክፍል የሚኖሩ ቤተሰቦች ማመልከቻ አስገብተው፣ ቢያንስ ነዋሪዎቹ በሰባ አምስት በመቶ (75%) ማመልከቻውን ከደገፉት፣ የፍጥነት መቀነሻ ሻኛዎች (Speed humps) ሊዘረጉ ይችላሉ። የፍጥነት መቀነሻ ሻኛ መዘርጋት ለመጠየቅ፣ ደንበኞች በ(202) 673- 6813 የደንበኛ አገልግሎት መስመር መደወል ይችላሉ።

 የአውቶቡስ ማቆምያ (ፌርማታ) ለውጥ ጥያቄዎች (Bus Stop Change Requests): የዲስትሪክት የመገናኛ ዲፓርትመንት፣ በዲስትሪክት ኦፍ ኮሎምብያ ባሉ ማቆምያዎች አዲስ የአውቶቡስ ማቆምያ እንዲደረግ፣ የአውቶቡስ ማቆምያ እንዲነሳ፣ የአውቶቡስ ማቆምያው ቦታ እንዲቀየር፣ እና ሌሎች የአውቶቡስ ማቆምያ መሻሻል ጥያቄዎች ይቀበላል። ማመልከቻው ለማቅረብ፣ ከታች ያለው የፒዲኤፍ (PDF) ፎርም፣ ወይም ጥያቄዎ የዜጎች አገልግሎት ጥያቄ ( Citizen Service Request) ማዕከል በመጎብኘት ከሚዘረጋው ማውጫ (dropdown menu) “የአውቶቡስ መቆምያ ለውጥ” (“Bus Stop Change”) የሚለው ጋር በመምረጥ በኤሌክትሮኒካዊ መንገድ ማቅረብ ይችላሉ።

 ድንገተኛ የዛፍ ማስወገድ (Emergency Tree Removal): ድንገተኛ የዛፍ ማስወገድ መጠየቅ ከፈለጉ እባክዎን 311 ይደውሉ።

 የብሎክ ፓርቲ ፈቃዶች (Block Party Permits): የብሎክ ፓርቲ ፈቃድ የሚጠይቁ ነዋሪዎች የቶፕስ (TOPS) tops.ddot.dc.gov በመጎብኘት ስለ ዝግጅቱ መረጃ በኦንላይን ማቅረብ ይችላሉ። ደንበኞች ማመልከቻው ለመሙላት ድጋፍ ከፈለጉ፣ የደንበኞች አገልግሎት መስመር (202) 673- 6813 ማናገር ይችላሉ።

 የህዝብ ቦታዎች ፈቃድ ማመልከቻዎች (Public Space Permit Applications): የህዝብ ቦታዎች የመጠቀም ወይም የመያዝ ፍቃዶች ማመልከቻዎች በ1100 4th Street, SW, 2ኛ ፎቅ በሚገኘው የፈቃዶች ማዕከል (Permitting Center) ከጠዋቱ 8፡30 እስከ ከሰአት 4፡15
ባሉ ሰዓታት፣ በሰኞ፣ ማክሰኞ፣ እሮብ፣ እና ዓርብ ማስረከብ ይቻላል። በሐሙስ፣ ሰዓታቱ ከጠዋቱ 9፡30 እስከ ከሰአቱ 4፡30 ይሆናል። የፈቃድ ቢሮ በሶስተኛ ፎቅ ነው የሚገኘው። አመልካቾች፣ ፈቃዶች እንዲሰጧቸው ለማመልከት ወደ ሁለተኛ ፎቅ መሄድ ይኖርባቸዋል። የተለያዩ የህዝብ ቦታ ፈቃዶች (Public Space Permits) ዓይነቶች የሚሰጡ አሉ።

 ጎዲሲጎ (goDCgo): ጎዲሲጎ (goDCgo) የዲዲኦቲ (DDOT) ተነሳሽነት ነው። ዲዲኦቲ (DDOT)፣ ሰዎችን እና እቃዎችን በዲሲ አከባቢ በተቻለ መጠን ንጽሕና እና ቅልጥፍና በተሞላበት መንገድ ለማጓጓዝ እንዲችሉ የሚያደርገው ቁርጠኝነት አካል ሲሆን፣ ጎዲሲጎ (goDCgo) የተፈጠረው ሰራተኞችን፣ ነዋሪዎችን እና ጎብኚዎችን በዲስትሪክት ለመጓጓዝ፣ መረጃ-መሰረት ያደረጉ ምርጫዎች ለማድረግ የሚያስችሉአቸው ትምህርት እና ድጋፍ ይሰጣል።
የጎዲሲጎ (goDCgo) ፕሮግራም፣ አንድ ሰው ይዘው የሚያጓጉዙ መኪኖች (single-occupant vehicle) በመቀነስ ያተኩራል፣ እንደነ ብስክሌት መጠቀም፣ በእግር መጓዝ፣ መኪና መጋራት (carpooling)፣ ቫን መጋራት (vanpooling) እና የሕዝብ መገናኛ (public transit) የመሳሰሉ በይበልጥ ዘላቂ የሆኑ የመገናኛ መንገዶች መጠቀምን ያበረታታል። ድህረገጻችን ወደ ከተማይቱ እንዴት መምጣት እንደሚችሉ እና እንዴት መዟዟር እንደሚችሉ የተለያዩ አማራጮች ይዘረዝራል፣ በተጨማሪ የርሶ ጉዞ በዲስትሪክቱ መንገዶች እና በአከባብያችን ያነሰ ተጽዕኖ በሚያደርግ መንገድ እንዴት ልዩ ጉዞዎን ወይም መደበኛ ጉዞዎን ማቀድ እንደሚችሉ የሚያግዙ የተለያዩ ምንጮች ያቀርባል።

ለተጨማሪ መረጃ እባክዎን http://www.godcgo.com ይጎብኙ

የትርጉም አገልግሎቶች:

ዲዲኦቲ (DDOT) ልዩ መስተንግዶዎችን እና የቋንቋ ድጋፍ አገልግሎቶች (የጽሑፍ ወይም የቃል) ያለ ክፍያ ያቀርባል። ልዩ መስተንግዶዎችን እና የቋንቋ ድጋፍ አገልግሎቶች ለማግኘት እባክዎን የሚከተለውን ያግኙ፦
ጆርዳይን ብሌይስ (Jordyne Blaise) በ [email protected] ወይም (202) 671-5117።

አድራሻ:

የዲስትሪክቱ የመገናኛ ዲፓርትመንት (District Department of Transportation) 55 M Street, SE, Suite 400 Washington, DC 20003 ስልክ: (202) 673-6813
ድህረገጽ፡ www.ddot.dc.gov